“መንግሥታትንና አሕዛብን ዕድል ፈንታ አድርገህ ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
ዘዳግም 2:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊዋጉን ወደ ኢያሳ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዎንና መላው ሰራዊቱ በያሀጽ ጦርነት ሊገጥሙን በወጡ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዎንም፥ እሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ ሊጋጠሙን ወደ ያሐጽ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሲሖንም ያለውን ሰው ሁሉ አሰልፎ በያሐጽ ከተማ አጠገብ ከእኛ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ። |
“መንግሥታትንና አሕዛብን ዕድል ፈንታ አድርገህ ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
እግዚአብሔርም፦ ‘የሐሴቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሴዎንንና ምድሩን በፊትህ በእጅህ አሳልፌ መስጠት እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛ ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ።
የእስራኤልም ልጆች የመቱአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ በኩል ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን ሀገራቸውን የወረሱአቸው የምድር ነገሥት እነዚህ ናቸው፤