ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
ዘዳግም 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወንድሞቻቸውም መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ እርሱ እንደ ተናገራቸው ርስታቸው እግዚአብሔር ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ርስታቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ጌታ ርስታቸው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንድሞቻቸው በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ርስታቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንድሞቻቸውም መካከል ርስት አይሆንላቸውም፤ እርሱ እንደተናገራቸው ርስታቸው እግዚአብሔር ነው። |
ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፤ የአምላካችንም አገልጋዮች ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፤ በሀብታቸውም ትመካላችሁ።
እግዚአብሔርም አሮንን አለው፥ “በምድራቸው ርስት አትወርስም፤ በመካከላቸውም ድርሻ አይሆንልህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ እንደ መሠዊያውና፥ በመጋረጃውም ውስጥ እንዳለው ሥርዐት ሁሉ ክህነታችሁን ጠብቁ፤ የሀብተ ክህነት አገልግሎታችሁንም አድርጉ፤ ከሌላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ስለዚህ ለሌዋውያን ከወንድሞቻቸው ጋር ክፍልና ርስት የላቸውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸው እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና።
ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልተሰጠም፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና፥ በኢያሪኮ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች እንዳካፈላቸው እንዲሁ ተካፈሉ።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤