La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለም​ሕ​ረ​ቱም የሚ​ገባ ትእ​ዛዝ ይህ ነው፤ ባል​ን​ጀ​ራህ ወይም ወን​ድ​ምህ የሚ​ከ​ፍ​ል​ህን ገን​ዘብ ሁሉ አት​ከ​ፈል፤ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ተብ​ላ​ለ​ችና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ እያንዳንዱ አበዳሪ ለእስራኤላዊ ባልንጀራው ያበደረውን ይተውለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ ምሕረት ዐውጇልና፣ አበዳሪው፣ እስራኤላዊ ባልንጀራውን ወይም ወንድሙን ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አፈጻጸሙም እንደሚከተለው ነው፤ ለእስራኤላዊ ወገኑ ገንዘብ ያበደረ ሁሉ ያበደረውን ብድር ይሰርዝለት፤ እግዚአብሔር የዕዳ መሰረዣ ዓመት ነው ብሎ ያወጀበት ዓመት ስለ ሆነ ከእስራኤላዊ ወገኑ ያበደረውን ገንዘብ ለመቀበል አይፈልግ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለምሕረቱም የሚገባ ወግ ይህ ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፤ የእግዚአብሔር ይቅርታ ታውጆአልና ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ አይሻ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 15:2
13 Referencias Cruzadas  

የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ ሸቀ​ጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገ​በዩ በሰ​ን​በት ቀን ቢያ​መጡ በሰ​ን​በት ወይም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀን ከእ​ነ​ርሱ አን​ገ​ዛም፤ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዓመት እና​ከ​ብ​ራ​ለን፤ ከሰ​ውም ዕዳ ማስ​ከ​ፈ​ልን እን​ተ​ዋ​ለን።


“ስለ ምን ጾምን፥ አን​ተም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ኸ​ንም? ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንስ ስለ ምን አዋ​ረ​ድን፥ አን​ተም አላ​ወ​ቅ​ኸ​ንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾ​ማ​ችሁ ቀን ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፥ ሠራ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ታስ​ጨ​ን​ቃ​ላ​ችሁ።


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ትም ባጡ ጊዜ ለሁ​ለ​ቱም ተወ​ላ​ቸው፤ እን​ግ​ዲህ ከሁ​ለቱ አብ​ልጦ ሊወ​ደው የሚ​ገ​ባው ማን​ኛው ነው?”


“በየ​ሰ​ባቱ ዓመት የዕዳ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ።


ከባ​ዕድ ግን በእ​ርሱ ዘንድ ያለ​ህን ሁሉ መቀ​በል ትች​ላ​ለህ፤ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ ያለ​ውን ሁሉ ግን ተው​ለት።


ሙሴም በዚ​ያች ቀን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት መጨ​ረሻ በም​ሕ​ረት ዓመት በዳስ በዓል፥


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።