የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
ዘዳግም 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በየሰባቱ ዓመት የዕዳ ምሕረትን ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ገንዘብ ያበደርካቸውን ሰዎች ሁሉ በየሰባተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ ዕዳቸውን በመሰረዝ ትተውላቸዋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ። |
የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን።
ስድስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ የተሸጠላችሁን፥ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ አርነት ታወጡታላችሁ፤ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
ለምሕረቱም የሚገባ ትእዛዝ ይህ ነው፤ ባልንጀራህ ወይም ወንድምህ የሚከፍልህን ገንዘብ ሁሉ አትከፈል፤ የአምላክህ የእግዚአብሔር ምሕረት ተብላለችና።
ሰባተኛው ዓመት የምሕረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አልሰጠውምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በልብህ እንዳታስብ ለራስህ ዕወቅ። ወንድምህም ዐይኑን በአንተ ላይ ያከፋል፤ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ይጮሃል፤ ኀጢአትም ይሆንብሃል።