ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አሰፋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከአንተም አስወጣቸዋለሁ።
ዘዳግም 14:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር ባርኮሃልና፥ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ አምላክህም እግዚአብሔር ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅብህ፥ ይህን ወደዚያ ለመሸከም ባትችል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ባርኮህ ሳለ፣ መንገዱ ቢርቅብህና እግዚአብሔር የስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ የሚመርጠው ስፍራ ከአንተ እጅግ ከመራቁ የተነሣ ዐሥራትህን ወደዚያ ቦታ ማድረስ ካልቻልህ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥ መንገዱ ቢርቅብህና ጌታ አምላክህ የስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ የሚመርጠው ስፍራ ከአንተ እጅግ ከመራቁ የተነሣ አሥራትህን ወደ እዚያ ቦታ ማድረስ ካልቻልክ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ እርሱ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን የመረጠው ቦታ ከአንተ በጣም ሩቅ በመሆኑ ለይተህ ያስቀመጥከውን ዐሥራት ለማጓጓዝ ቢያስቸግርህ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ ጊዜ፥ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ አምላክህም እግዚአብሔር ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅብህ፥ ይህን ወደዚያ ለመሸከም ባትችል፥ ትሸጠዋለህ፥ |
ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አሰፋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከአንተም አስወጣቸዋለሁ።
የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም፥ ከአንጢሊባኖስም፥ ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።
አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከአንተ ሩቅ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከላምና ከበግ መንጋህ እንዳዘዝሁህ እረድ፤ ሰውነትህም የወደደችውን በሀገርህ ውስጥ ብላው።
ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከከተሞቻችሁ ሁሉ በአንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደዚያም ትመጣላችሁ።