ዘዳግም 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ ጋር አትተባበር፤ አትስማውም፤ ዐይንህም አይራራለት፤ አትማረውም፤ አትሸሽገውም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕሺ አትበለው፤ ወይም አታድምጠው፤ አትራራለት፤ አትማረው፤ ወይም አትሸሽገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሺ አትበለው፤ ወይም አታዳምጠው፤ አትራራለት፤ አትማረው፤ ወይም አትሸሽገው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እንደዚህ ያለውን ሰው ያግባባህ ዘንድ አትፍቀድለት፤ የሚናገረውን እንኳ አታድምጥ፤ ምሕረትም ሆነ ርኅራኄ በማድረግ ሕይወቱን ለማዳን አትሞክር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ አትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ |
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም።
ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥
እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን ታመልካለህ።
ለእግዚአብሔር ያይደለ ለአጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ ድንገት ለተገኙ ለማይሠሩና ለማይጠቅሙ አማልክት፥ አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው አማልክት ሠዉ።
አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓሊምንና አስታሮትን፥ የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፤ አላመለኩትምም።