Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነገር ግን ንጹ​ሑን ደም ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አትራራለት፤ ነገር ግን መልካም እንዲሆንልህ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አትራራለት፤ ነገር ግን መልካም እንዲሆንልህ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግድ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለእርሱ ምንም ምሕረት አታድርግለት፤ በሁሉ ነገር መልካም ይሆንልህ ዘንድ ነፍሰ ገዳይን ከእስራኤል አስወግድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዓይንህ አትራራለት፤ ነገር ግን መልካም ይሆንልህ ዘንድ ንጹሑን ደም ከእስራኤል ታስወግዳለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 19:13
17 Referencias Cruzadas  

የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”


በዳ​ዊ​ትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተ​ከ​ታ​ታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳ​ኦ​ልና በቤቱ ላይ ደም አለ​በት፥”


የሳ​ኦ​ልን አጥ​ን​ትና የል​ጁን የዮ​ና​ታ​ንን አጥ​ንት፥ የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ት​ንም ሰዎች አጥ​ንት በብ​ን​ያም በአ​ባቱ በቂስ መቃ​ብር አጠ​ገብ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ። ከዚ​ያም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ርን ሰማት።


ንጉ​ሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገ​ረህ አድ​ርግ፤ ገድ​ለ​ህም ቅበ​ረው፤ ኢዮ​አ​ብም በከ​ንቱ ያፈ​ሰ​ሰ​ውን ደም ከእ​ኔና ከአ​ባቴ ቤት ታር​ቃ​ለህ።


በተ​ወ​ለ​ድ​ሽ​በት ቀን ከሰ​ው​ነ​ትሽ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ በሜዳ ላይ ተጣ​ልሽ እንጂ፥ ከዚህ አን​ዳች ይደ​ረ​ግ​ልሽ ዘንድ ዐይኔ አል​ራ​ራ​ል​ሽም፤ ማንም አላ​ዘ​ነ​ል​ሽም።


ሰውን የገ​ደለ ሰው ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሰው​ንም የመ​ታና የገ​ደለ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ሞት የተ​ፈ​ረ​ደ​በ​ትን ነፍሰ ገዳ​ዩ​ንም ለማ​ዳን የነ​ፍስ ዋጋ አት​ቀ​በሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ከእ​ርሱ ጋር አት​ተ​ባ​በር፤ አት​ስ​ማ​ውም፤ ዐይ​ን​ህም አይ​ራ​ራ​ለት፤ አት​ማ​ረ​ውም፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ውም፤


የከ​ተ​ማው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይል​ካሉ፤ ከዚ​ያም ይይ​ዙ​ታል። በባ​ለ​ደ​ሙም እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይሞ​ታ​ልም።


ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነፍስ በነ​ፍስ፥ ዐይን በዐ​ይን፥ ጥርስ በጥ​ርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእ​ግር ይመ​ለ​ሳል።


አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ባደ​ረ​ግህ ጊዜ የን​ጹ​ሑን ደም በደል ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ታር​ቃ​ለህ።


እጅ​ዋን ቍረጥ፤ ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ላት።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የአ​ሕ​ዛብ ምርኮ ትበ​ላ​ለህ፤ ዐይ​ን​ህም አታ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ ያም ለአ​ንተ ክፉ ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አታ​ም​ል​ካ​ቸው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ በሰ​ጣ​ቸ​ውና በመ​ታ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos