ዘዳግም 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት ከሰጠህ ከተሞች በአንዲቱ ከተማህ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባቸው ከሰጠህ ከተሞች በአንደኛዋ ውስጥ አንዳንድ ወራዶች ሰዎች ከመካከልህ ተነሥተው ነዋሪዎቹን ወደማታውቃቸው ወደ ሌሎች አማልክት ‘እንሂድና እናምልክ’ ብለው ወደ ጥፋት መንገድ መርተው መውሰዳቸውን ትሰማ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት በሚሰጥህ በአንዲቱ ከተማህ፦ ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቍቸውን ሌሎችን አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥ |
ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።