አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከአንተ ሩቅ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከላምና ከበግ መንጋህ እንዳዘዝሁህ እረድ፤ ሰውነትህም የወደደችውን በሀገርህ ውስጥ ብላው።
ዘዳግም 12:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ እንዲሁ ብላው፤ ከአንተ ንጹሕ ሰው፥ ንጹሕም ያልሆነ ይብላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚዳቋ ወይም ድኵላ እንደሚበላ አድርገህ ብላ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆኑትና ያልሆኑት ሊበሉ ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚዳቋ ወይም ድኩላ እንደሚበላ አድርገህ ብላ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ መብላት ይችላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነጻም ሆነ ያልነጻ ማንኛውም ሰው የአጋዘንም ሆነ የሚዳቋ ሥጋ በሚበላው ዐይነት ያንን ሥጋ መብላት ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚዳቍና ዋላ እንደሚበሉ እንዲሁ ብላው፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ ይብላው። |
አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከአንተ ሩቅ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከላምና ከበግ መንጋህ እንዳዘዝሁህ እረድ፤ ሰውነትህም የወደደችውን በሀገርህ ውስጥ ብላው።