ዘዳግም 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች ሁሉ ዐይኖቻችሁ አይተዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእናንተ ዐይኖች ግን እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእናንተ ዐይኖች ግን ጌታ ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያደረጋቸውን እነዚህን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ በዐይናችሁ ያያችሁ እናንተ ራሳችሁ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረጋትን ታላቂቱን ሥራ ሁሉ ዓይኖቻችሁ አይተዋል። |
በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንም፥ ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ሁሉ፤
“በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበዙም ዘንድ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ዮርዳኖስን የምትሻገሩላትን ምድር እንድትወርሷት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ጠርቶ አላቸው፥ “እግዚአብሔር በፊታችሁ በግብፅ ምድር፥ በፈርዖንና በሹሞቹ ሁሉ፥ በምድሩም ሁሉ ያደረገውን ሁሉ፥
ብዔልፌጎርን የተከተለውን ሰው ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ለይቶ አጥፍቶታልና አምላካችሁ እግዚአብሔር በብዔልፌጎር ያደረገውን ዐይኖቻችሁ አይተዋል።
እግዚአብሔር ዛሬ በዚህ በሕይወት ካላችሁት ከእናንተ ከሁላችሁ ጋር እንጂ ከአባቶቻችሁ ጋር ይህችን ቃል ኪዳን አላጸናም።
አምላክህ እግዚአብሔር ዓይንህ እያየች፥ ታላቅ መቅሠፍትን፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ የጸናችውንም እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።
ኢያሱ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ፥ እስራኤል እግዚአብሔርን አመለኩ።