እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
ዘዳግም 11:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ! እኔ ዛሬ ከበረከትና ከመርገም አንዱን እንድትመርጡ ዕድል እሰጣችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ |
እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”
“እንዲህም ይሆናል፤ እኔ በፊትህ ያኖርሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረከቱና መርገሙ በወረደብህ ጊዜ፥ አምላክህ እግዚአብሔር በሚበትንህ በዚያ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ሆነህ በልብህ ዐስበው፤