አክዓብም አብድዩን፥ “በሀገሩ መካከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እንሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኝ እንደ ሆነ” አለው።
ዘዳግም 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳህ ለእንስሶችህ ሣርን ይሰጣል፤ ትበላማለህ፤ ትጠግብማለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንስሶችህ የሚመገቡት ሣር ይበዛላችኋል፤ የሚያስፈልግህን ምግብ ሁሉ ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳ ለእንስሶችህ ሣርን እሰጣለሁ፥ ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ። |
አክዓብም አብድዩን፥ “በሀገሩ መካከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እንሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኝ እንደ ሆነ” አለው።
እንግዲህ ለራሳችን ምን እንሰብስብ? የእንስሳት ጠባቂዎች አለቀሱ፤ ማሰማሪያ የላቸውምና፥ የበጎች መንጋዎችም ጠፍተዋልና።
እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፥ “እነሆ እህልንና ወይንን፥ ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።
እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ! የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኀይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።
ብዙ መብል ትበላላችሁ፤ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።
የእህሉም ማበራየት በእናንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቈረጥ ይደርሳል፤ የወይኑም መቈረጥ እስከ እህሉ መዝራት ይደርሳል፤ እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ ተዘልላችሁ ትኖራላችሁ።
ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።
ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጕድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ፤