ዘዳግም 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ለሌዋውያን ከወንድሞቻቸው ጋር ክፍልና ርስት የላቸውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸው እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋዊ በወንድሞቹ መካከል ድርሻም ሆነ ርስት የሌለው ከዚህ የተነሣ ነው፤ አምላክህ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ርስቱ እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ጌታ ርስቱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሌዊ ነገድ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ርስት እንዲኖረው ያልተደረገበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ አስቀድሞ እንደ ተናገረ ካህናት ሆነው የማገልገልን መብት በማግኘታቸው ራሱ እግዚአብሔር ለሌዋውያን ርስታቸው ነው።) መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው እግዚአብሔር ርስቱ ነው። |
ከአንድ ወርም ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።
እናንተም፥ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁም፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ ውስጥ የተቀመጠው ሌዋዊም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
ሌዋዊዉም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በከተማህ ውስጥ ያለ መጻተኛ፥ ድሃ-አደግም፥ መበለትም መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው።
ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።