ሁለተኛውንም በምልክቱ ስትነፉ በአዜብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ ሦስተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በባሕር በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ አራተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በመስዕ በኩል የሰፈሩት ሠራዊት ይጓዙ፤ ለማስጓዝ በምልክት ትነፉታላችሁ።
ዘዳግም 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤልም ልጆች የማስቢ ወገን ከሚሆን ከኢያቅም ልጆች ቦታ ከቤሮስ ተጓዙ። በዚያም አሮን ሞተ፤ ተቀበረም፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ከብኤሮት ብኔያዕቃን፣ (ከያዕቃን ልጆች የውሃ ጕድጓዶች) ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤ ልጁ አልዓዛር በርሱ ምትክ ካህን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላዊያንም ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም እዚያ ሞቶ፥ እዚያው ተቀበረ፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (እስራኤላውያንም ከቤን ያዕቃን የውሃ ጒድጓዶች ተነሥተው ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ አሮንም በዚያው ሞቶ ተቀበረ፤ በእርሱም ምትክ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ፤ በዚያም አሮን ሞተ በዚያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆነ። |
ሁለተኛውንም በምልክቱ ስትነፉ በአዜብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ ሦስተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በባሕር በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ አራተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በመስዕ በኩል የሰፈሩት ሠራዊት ይጓዙ፤ ለማስጓዝ በምልክት ትነፉታላችሁ።
ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።