Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ተመ​ል​ሼም ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ጽላ​ቱ​ንም በሠ​ራ​ሁት ታቦት ውስጥ አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ ኖሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም ከተራራው ተመልሼ ወረድሁ፤ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት በሠራሁት ታቦትም ውስጥ፣ ጽላቱን አስቀመጥኋቸው፤ አሁንም እዚያ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፥ ጌታም እንዳዘዘኝ በዚያ ይገኛሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እኔም ከተራራው ተመልሼ በመውረድ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን በሠራሁት ታቦት ውስጥ አኖርኳቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እነሆ፥ በዚያው ውስጥ ይገኛሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 10:5
10 Referencias Cruzadas  

በታ​ቦ​ቱም ውስጥ እኔ የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።


የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ሰ​ጥ​ህን ምስ​ክር በታ​ቦቱ ውስጥ ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


ሙሴም ተመ​ለሰ፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ስ​ክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተ​ራ​ራው ወረደ፤ የድ​ን​ጋይ ጽላ​ቱም በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለት ወገን ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።


በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወ​ረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተ​ራ​ራው በወ​ረደ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ሲነ​ጋ​ገር ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ አላ​ወ​ቀም ነበር።


ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው።


በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃሎች ሁሉ በእ​ነ​ዚህ ጽላት እጽ​ፋ​ለሁ፤ በታ​ቦ​ቱም ውስጥ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ አለኝ።


እኔም ተመ​ልሼ ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ሁለ​ቱም የቃል ኪዳን ጽላት በሁ​ለቱ እጆች ነበሩ።


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos