አሞጽ 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሲኦል ቢወርዱ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ ወደ ሰማይም ቢወጡ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቃብር በጥልቀት ቈፍረው ቢወርዱም፣ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ ወደ ሰማይ ቢወጡም፣ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወደ ሲኦል ቢወርዱ እንኳ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ ወደ ሰማይም ቢወጡ እንኳ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድርን ቆፍረው ወደ ሙታን ዓለም ቢወርዱ እንኳ እኔ ከዚያ መንጥቄ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ሰማይም መጥቀው ቢወጡ እንኳ እኔ መልሼ አወርዳቸዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሲኦል ቢወርዱ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፥ ወደ ሰማይም ቢወጡ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፥ |
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ያገቡአቸዋል።
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር ወደ ቀደሙት ሕዝብ አወርድሻለሁ። በምድርም ላይ በሕይወትሽ ጸንተሽ እንዳትኖሪም ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ቀድሞ በፈረሰው ቤት ከምድር በታች አኖርሻለሁ።
በውኃው አጠገብ ያሉ የዕንጨቶች ሁሉ ቁመት እንዳይረዝም ራሱም ወደ ደመና እንዳይደርስ ያንም ውኃ የሚጠጡት እንጨቶች ሁሉ በርዝመታቸው ከእርሱ ጋራ እንዳይተካከሉ ሁሉም ወደ መቃብር በሚወርዱ ሰዎች መካከል በጥልቅ ምድር ሞቱ።