Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አሞጽ 9:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ምድርን ቆፍረው ወደ ሙታን ዓለም ቢወርዱ እንኳ እኔ ከዚያ መንጥቄ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ሰማይም መጥቀው ቢወጡ እንኳ እኔ መልሼ አወርዳቸዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 መቃብር በጥልቀት ቈፍረው ቢወርዱም፣ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ ወደ ሰማይ ቢወጡም፣ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ወደ ሲኦል ቢወርዱ እንኳ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ ወደ ሰማይም ቢወጡ እንኳ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ እጄ ከዚያ ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ ወደ ሰማ​ይም ቢወጡ ከዚያ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወደ ሲኦል ቢወርዱ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፥ ወደ ሰማይም ቢወጡ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 9:2
15 Referencias Cruzadas  

ባቢሎን ወደ ሰማይ ብትወጣ ከፍተኛውን ምሽግዋን ብታጠናክር እንኳ የሚደመስሳትን አጥፊ እልካለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ነገር ግን እንደ ንስር ወደ ላይ ብትበር፥ መኖሪያህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ። ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንደ መብረቅ ተወርውሮ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁት፤


አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።”


እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚመጣበት ጊዜ ከቊጣውና ከአስፈሪ ግርማው ለማምለጥ በአለት ዋሻና በመሬት ንቃቃት ውስጥ ለመሸሸግ ይሞክራሉ።


የሙታን ዓለም በእግዚአብሔር ፊት ግልጥልጥ ያለ ነው፤ ምንም ነገር ሊሸፍነው አይችልም።


ክፉ ሰው ምንም እንኳ በትዕቢቱ እስከ ሰማይ ከፍ ቢልም ዐናቱም ደመናን ቢነካ


ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፤ ድቅድቅ ጨለማ ከቶ የለም።


ወደ ሙታን ዓለም ወርደሽ በጥንት ዘመን ይኖሩ ከነበሩ ሕዝቦች ጋር እንድትደባለቂ አደርጋለሁ፤ ከሙታን ጋር ተወዳጅተሽ እንድትኖሪ በዚያ ከምድር በታች ባለ ዓለም ውስጥ ዘለዓለም ፈራርሰው ከቀሩ ነገሮች ጋር እተውሻለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ዳግመኛ ሰው አይኖርብሽም፤ በሕያዋንም ምድር ለመኖር ቦታ የለሽም፤


የቱንም ያኽል ውሃ እየጠጣ ቢያድግ በዚህ ዐይነት ከፍተኛ ቁመት እስከ ደመና የሚደርስ ዛፍ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አይኖርም። ሟቾች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት ፍርድ በእነርሱም ላይ ይደርሳል፤ ወደ ሙታን ዓለምም ይወርዳሉ።”


አንተ ግን ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል? ከድቅድቅ ጨለማ ባሻገር ሆኖ እንዴት ሊፈርድብን ይችላል?


እግዚአብሔር በሰላም እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም እንኳ የሚሄዱበትን መንገድ ሁሉ አተኲሮ ይመለከታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios