አሞጽ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ኤማትራባ እለፉ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይበረታሉ፤ ድንበራቸውም ከድንበራቸው ይሰፋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጋትም ውረዱ፤ እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታታችሁ ይሻላሉን? የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ካልኔ እለፉና ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስቲ ወደ ካልኔ ከተማ ሄዳችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም አልፋችሁ “ሐማት” ተብላ ወደምትጠራው ታላቂቱ ከተማና የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋት ውረዱ፤ እናንተ ከእነርሱ ትበልጣላችሁን? ግዛታችሁስ ከእነርሱ ግዛት ይበልጣልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ካልኔ አልፋችሁ ተመልከቱ፥ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፥ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን? |
በዚያም ዘመን ሰሎሞን፥ ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኤማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠራው ቤት ውስጥ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እየበሉና እየጠጡ፥ ደስታም እያደረጉ ሰባት ቀን በዓሉን አከበሩ።
የአሦርም ንጉሥ ከባቢሎንና ከኩታ፥ ከአዋና ከሐማት፥ ከሴፌርዋይም ሰዎችን አመጣ፤ በእስራኤልም ልጆች ፋንታ በሰማርያ ከተሞች አኖራቸው፤ ሰማርያንም ወረሱአት፤ በከተሞችዋም ተቀመጡ።
የኤማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፋሩዋይምና የሄና የዒዋም አማልክት ወዴት አሉ? ስማርያን ከእጄ አድነዋታልን?
ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትን ቅጥር፥ የኢያቢስንም ቅጥር፥ የአዛጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም ሀገር ከተሞችን ሠራ።
“ስለ ደማስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ፤ ቀለጡም፤ እንደ ባሕርም ተነዋወጡ፤ ያርፉም ዘንድ አይችሉም።
አንቺ በመስኖች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን?
እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለ ያ አርበኛ ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፤ ቀድሞ የተናገረውንም ቃል ተናገረ፤ ዳዊትም ሰማ።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ላኩአት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣች ጊዜ አስቀሎናውያን፥ “እኛንና ሕዝባችንን ልታስገድሉን የእስራኤልን አምላክ ታቦት ለምን አመጣችሁብን?” ብለው ጮኹ።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፥ “በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎችም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእስራኤል አምላክ ታቦትም ወደ ጌት ሄደች።