የቀረውም የአክዓብ ነገር፥ ያደረገውም ነገር ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የሠራው ቤት፥ የሠራቸውም ከተሞች ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
አሞጽ 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክረምቱንና የበጋዉን ቤት እመታለሁ፤ በዝሆንም ጥርስ የተለበጡት ቤቶች ይጠፋሉ፤ ሌሎችም ታላላቆች ቤቶች ይፈርሳሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክረምቱን ቤት፣ ከበጋው ቤት ጋራ እመታለሁ፤ በዝኆን ጥርስ ያጌጡ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፤ ታላላቅ አዳራሾችም ይፈርሳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክረምቱንና የበጋውን ቤት እመታለሁ፤ በዝሆንም ጥርስ የተለበጡት ቤቶች ይጠፋሉ፥ ታላላቅም ቤቶች ይፈርሳሉ፥” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክረምቱንና የበጋውን ወራት የሚያሳልፉባቸውን ቤቶች ሁሉ እደመስሳለሁ፤ በዝሆን ጥርስ አጊጠው የተሠሩ ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ይወድማሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክረምቱንና የበጋውን ቤት እመታለሁ፥ በዝሆንም ጥርስ የተለበጡት ቤቶች ይጠፋሉ፥ ታላላቆችም ቤቶች ይፈርሳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
የቀረውም የአክዓብ ነገር፥ ያደረገውም ነገር ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የሠራው ቤት፥ የሠራቸውም ከተሞች ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
ይህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰምቶአልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆናሉ፤ ታላላቅና የሚያምሩ ቤቶችም የሚቀመጥባቸው አይኖርም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአለው ዙሪያሽ ድረስ ምድርሽ ይጠፋል፥ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፤ ሀገሮችሽም ይበዘበዛሉ።”
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ኤዶምያስ፦ እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፣ በሰዎችም ዘንድ፦ የበደል ዳርቻና እግዚአብሔር ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ይባላል።
ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም።