አሞጽ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስከ ጢሮስ በአለው ዙሪያሽ ድረስ ምድርሽ ይጠፋል፥ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፤ ሀገሮችሽም ይበዘበዛሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጠላት ምድሪቱን ይወርራል፤ ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁን ይዘርፋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ምድሪቱን በዙርያዋ ጠላት ይከባታል፤ ምሽግሽንም ከአንቺ ያፈርሳል፥ የንጉሥ ቅጥሮችሽም ይበዘበዛሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጠላት አገራቸውን ይከባል፤ ምሽጎቻቸውንም አፈራርሶ ቤቶቻቸውን ይዘርፋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በምድሪቱ ዙሪያ ጠላት ይመጣል፥ ብርታትሽንም ከአንቺ ያወርዳል፥ አዳራሾችሽንም ይበዘበዛሉ። |
በዘመኑም የአሶር ንጉሥ ፎሐ በምድሪቱ ላይ ወጣ፤ ምናሔምም የፎሐ እጅ ከእርሱ ጋር እንዲሆን አንድ ሺህ መክሊት ብር ሰጠው።
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሰ፤ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠለ፤ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፋ።
የክረምቱንና የበጋዉን ቤት እመታለሁ፤ በዝሆንም ጥርስ የተለበጡት ቤቶች ይጠፋሉ፤ ሌሎችም ታላላቆች ቤቶች ይፈርሳሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“የእስራኤል ቤት ሆይ እነሆ እኔ የሚያስጨንቋችሁን ሕዝብ አስነሣባችኋለሁ፥” ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር፤ እነርሱም ከሐማት መግቢያ ጀምረው እስከ ዐረባ ወንዝ ድረስ ትገቡ ዘንድ አይፈቅዱላችሁም።
ጌታ እግዚአብሔር፥ “የያዕቆብን ትዕቢት አረክሳለሁ፤ ሀገሮቹንም ጠላሁ፤ ከተሞቹንም ከሚኖሩባቸው ሰዎች ጋር አጠፋለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአልና።