እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
አሞጽ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀስተኛውም አይቆምም፤ ፈጣኑም አያመልጥም፤ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስተኛው በቦታው ጸንቶ አይቆምም፤ ፈጣኑም ተዋጊ ሮጦ አያመልጥም፤ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስተኛውም አይቆምም፥ ፈጣኑም ሯጭ አያመልጥም፥ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስት ወርዋሪዎች ቆመው አይመክቱም፤ ፈጣን ሯጮችም ሮጠው አያመልጡም፤ ፈረሰኞችም ሕይወታቸውን ማዳን አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈጣኑም አይድንም፥ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም፥ |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
ጥፋት በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ተዋጊዎችዋ ተያዙ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ተበቅሎአቸዋልና፥ እግዚአብሔርም ፍዳን ከፍሎአቸዋልና።
ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ እጥልሃለሁ።
እግዚአብሔርን በመሠውያው ላይ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “አበቦች የተሳሉባቸውን ምሰሶዎችን ምታ፤ መድረኮቹም ይናወጣሉ፤ ራሳቸውንም ቍረጥ፤ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፤ ከሚሸሹትም የሚያመልጥ የለም፤ ከሚያመልጡትም የሚድን የለም።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።