ሐዋርያት ሥራ 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ ሰው እኮ በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳንህ ላይ ምን ያህል ጕዳት እንዳደረሰ ከብዙ ሰው ሰምቻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐናንያም መልሶ “ጌታ ሆይ! በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐናንያ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! ይህ ሰው በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ምእመናንህ ላይ ብዙ ክፉ ነገር ማድረጉን ከብዙዎች ሰምቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐናንያም መልሶ፦ “ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤ |
ይህን ትምህርት የሚከተሉ ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰርሁ ወደ ወህኒ ቤት አሳልፌ በመስጠት እስከ ሞት ድረስ አሳደድኋቸው።
ሳውል ግን ገና አብያተ ክርስቲያናትን ይቃወም ነበር፤ የሰውንም ቤት ሁሉ ይበረብር ነበር፤ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።
የሰሙትም ሁሉ አደነቁ፤ እንዲህም አሉ፥ “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ ይጠላቸው የነበረው ይህ አይደለምን? ስለዚህ ወደዚህ የመጣው እያሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን?”
በሮሜ ላላችሁ፥ እግዚአብሔር ለሚወዳችሁ፥ ለመረጣችሁና ላከበራችሁ ሁሉ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ይኸውም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳንን በአገልግሎቴ ደስ አሰናቸው ዘንድ በይሁዳ ሀገር ካሉ ዐላውያን እንዲያድነኝ ነው።
ለቅዱሳንም እንደሚገባ በጌታችን ተቀበሉአት፤ እርስዋ ለብዙዎች፥ ለእኔም ረዳት ናትና፤ ለችግራችሁም በፈቀዳችሁት ቦታ መድቡአት።
በቆሮንቶስ ሀገር ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለከበሩና ቅዱሳን ለተባሉ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ለሚጠሩ ሁሉ፥
ይህንም የምላችሁ ስዘልፋችሁ ነው፤ እንግዲህ ከመካከላቸሁ ወንድማማቾችን ከወንድሞቻቸው ጋር ማስታረቅ የሚችል ሽማግሌ የለምን?
በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ በኤፌሶን ላሉ ቅዱሳን፥
ከኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ፤ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፤
በቈላስይስ ላሉ ቅዱሳንና በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ወንድሞቻችን፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
ሳሙኤልም፥ “እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።