ሐዋርያት ሥራ 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፥ “የእግዚአብሔርን ጸጋ በገንዘብ ልትገዛ ዐስበሃልና ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለመግዛት አስበሃልና፣ አንተም ገንዘብህም ዐብራችሁ ጥፉ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት በማሰብህ ገንዘብህ ካንተ ጋር ይጥፋ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። |
እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገንዘብም የሌላችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ጠጡ።
እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።
ከዚህም በኋላ ይህ ሰው በዐመፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በምድር ላይም በግንባሩ ወደቀና ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።
እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለአመንነው ለእኛ እንደ ሰጠን፥ ያን ጸጋውን እንደ እኛ አስተካክሎ ከሰጣቸው እግዚአብሔርን ልከለክል የምችል እኔ ማነኝ?”
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ ኀጢአታችሁም ይሰረይላችኋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ትቀበላላችሁ።
ሰባተኛው ዓመት የምሕረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አልሰጠውምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በልብህ እንዳታስብ ለራስህ ዕወቅ። ወንድምህም ዐይኑን በአንተ ላይ ያከፋል፤ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ይጮሃል፤ ኀጢአትም ይሆንብሃል።
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።