ሐዋርያት ሥራ 7:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱና አባቶቻችንም በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ፊት አስወጥቶ ወደ ሰደዳቸው ወደ አሕዛብ ሀገር ከእነርሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችንም ድንኳኗን ከተቀበሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት ያሳደዳቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ ይዘዋት ገቡ፤ እስከ ዳዊትም ዘመን ድረስ በምድሪቱ ተቀመጠች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከፊታቸው ያባረረላቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ አባቶቻችን ይህችን የተቀበሉአትን ድንኳን ከኢያሱ ጋር ወደዚያ አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ እዚያ ኖረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። |
ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥
ሙሴም በምድረ በዳ የሠራት የእግዚአብሔር ማደሪያና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ በዚያን ጊዜ በገባዖን ባለው በኮረብታው መስገጃ ነበሩ።
እነርሱም ወረሱአት፤ በከነዓን ምድር የሚኖሩትንም ሰዎች በፊታቸው አጠፋሃቸው፤ የሚወድዱትንም ነገር ያደርጉባቸው ዘንድ እነርሱንና ነገሥታቶቻቸውን፥ የምድሩንም አሕዛብ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
“በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፤ በዚያም የምስክሩን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
እርሱ እግዚአብሔር ታላላቆችንና ኀይለኞችን አሕዛብ ከፊታችሁ ያጠፋቸዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የተቋቋማችሁ በፊታችሁ ማንም የለም።
እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ፥ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞሬዎናውያንን ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
ሕዝቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪሩቤልም ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።