የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
ሐዋርያት ሥራ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እግዚአብሔር በእጁ ድኅነትን እንደሚያደርግላቸው የሚያስተውሉ መስሎት ነበር፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወገኖቹም እግዚአብሔር በርሱ እጅ ነጻ እንደሚያወጣቸው የሚያስተውሉ መስሎት ነበር፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹም እግዚአብሔር በእጁ መዳንን እንዲሰጣቸው የሚያስተውሉ ይመስለው ነበር፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ነጻ እንደሚያወጣቸው ወገኖቹ የሚገነዘቡ መስሎት ነበር፤ እነርሱ ግን ይህን አልተገነዘቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹም እግዚአብሔር በእጁ መዳንን እንዲሰጣቸው የሚያስተውሉ ይመስለው ነበር፥ እነርሱ ግን አላስተዋሉም። |
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
እነርሱ ግን፤ ከተናገራቸው ያስተዋሉት የለም፤ ይህ ነገር ከእነርሱ የተሰወረ ነበርና፤ የተናገረውንም አያውቁም ነበርና።
እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉትም፤ እንዳይመረምሩት ከእነርሱ የተሰወረ ነውና፤ ስለዚህ ነገርም እንዳይጠይቁት ይፈሩት ነበርና።
አንጾኪያም በደረሱ ጊዜ ምእመናኑን ሁሉ ሰብስበው እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ሁሉ፥ ለአሕዛብም የሃይማኖትን በር እንደ ከፈተላቸው ነገሩአቸው።
ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም ምእመናንና ሐዋርያት፥ ቀሳውስትም ተቀበሉአቸው፤ እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ያደረገላቸውን ነገሩአቸው።
ብዙ ክርክርም ከተከራከሩ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአሕዛብ ከአፌ የወንጌሉን ቃል እንዳሰማቸውና እንዲያምኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ መረጠኝ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
ጳውሎስም ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ በእርሱ ሐዋርያነት እግዚአብሔር በአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ነገራቸው።
በማግሥቱም ከመካከላቸው ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኘ፤ ሊያስታርቃቸውም ወድዶ፦ ‘እናንተማ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ለምን ትጣላላችሁ?’ አላቸው።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለሁበት አለሁ፤ ለእኔም የሰጠኝ ጸጋው ለከንቱ የሆነብኝ አይደለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደረው የእግዚአብሔር ጸጋ አጸናኝ እንጂ እኔ አይደለሁም።
በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።
ከእርሱም ጋር አብረን እየሠራን፥ የተቀበላችኋትን የእግዚአብሔር ጸጋ ለከንቱ እንዳታደርጓት እንማልዳችኋለን።
እነርሱም፥ “አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል” አሉት። ሶምሶንም፥ “እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ፤ ለእነርሱም አሳልፋችሁ ስጡኝ፤ እናንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላቸው።
ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም።
ነፍሱንም በእጁ ጥሎ ፍልስጥኤማዊዉን ገደለ፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ታላቅ መድኀኒት አደረገ፤ እስራኤልም ሁሉ አይተው ደስ አላቸው፤ በከንቱ ዳዊትን ትገድለው ዘንድ ስለምን በንጹሕ ደም ላይ ትበድላለህ?”