ሐዋርያት ሥራ 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የግብፅን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በሚናገረውና በሚሠራውም ሁሉ ብርቱ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በንግግሩና በተግባሩም ብርቱ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የግብጾችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም የግብጻውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ። |
የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ይሆናሉ፤ ነገሥታትን የሚመክሩ ጥበበኞችም ምክራቸው ስንፍና ትሆናለች። ንጉሥን፥ “እኛ የጥበበኞች ልጆች፥ የቀደሙ ነገሥታትም ልጆች ነን እንዴት ትሉታላችሁ?”
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህ ምንድነው?” አላቸው፤ እነርሱም እንዲህ አሉት፥ “በእግዚአብሔር ፊትና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በቃሉና በሥራው ብርቱ ነቢይና እውነተኛ ሰው ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፥