ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ሐዋርያት ሥራ 4:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያመኑትም ሁሉ አንድ ልብና አንዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በውስጣቸውም የሁሉ ገንዘብ በአንድነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገንዘብ ነው” የሚል አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያመኑትም ሁሉ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ነበር፤ ያላቸውም ሁሉ የጋራ ነበር እንጂ የራሱ የሆነውን ሀብት እንኳ እንደ ግሉ የሚቈጥር ማንም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማኞች ሁሉ አንድ ልብና አንድ አሳብ ነበራቸው፤ ማንም ሰው “ይህ የእኔ ነው” የሚለው ነገር አልነበረውም፤ በመካከላቸውም ሁሉ ነገር የጋራ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም። |
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
እንግዲህ በዓለም አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ይኖራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስምህ ጠብቃቸው፤
በሐዋርያት እጅም በሕዝቡ ዘንድ ተአምራትና ድንቅ ሥራዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅደስም በሰሎሞን መመላለሻ በአንድነት ነበሩ።
እንዲሁ ሁላችን ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፤ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው አካሎች ነን፤ ስጦታውም ልዩ ልዩ ነው፤
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
ወድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ደስ ይበላችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአንድ ልብም ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የሰላምና የፍቅር አምላክም ከእናንተ ጋር ይሁን።
ነገር ግን ምናልባት የመጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳልኖርም ቢሆን በወንጌል ሃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስና በአንድ አካል ጸንታችሁ እንደምትኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራችሁ ለክርስቶስ ትምህርት እንደሚገባ ይሁን።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።