በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
ሐዋርያት ሥራ 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሎም ቆመ፤ እየሮጠና እየተራመደም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደስ ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘልሎም ቀጥ ብሎ ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ወዲህ ወዲያ እየሄደና እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋራ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፤ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብድግ ብሎም ቆመ፤ እየተራመደም ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ እየተራመደና እየዘለለም እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ። |
በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
በዚያን ጊዜም አየ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፤ ተከተለውም፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
ያንጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ በደስታም ዝለሉ፤ ዋጋችሁ በሰማይ ብዙ ነውና፤ አባቶቻቸውም ነቢያትን እንዲሁ አድርገዋቸው ነበርና።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ያን የዳነውን ሰው በቤተ መቅደስ አገኘውና፥ “እነሆ፥ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” አለው።
ያም ክፉ መንፈስ የያዘው ሰው ተነሣባቸው፤ አየለባቸውም፤ አሸነፋቸውም፤ አቍስሎም ከዚያ ቤት አስወጥቶ አባረራቸው።