ከዚህ በኋላ ተጋግዘን በገመድ አጠናከርናት፤ ከዚህም ቀጥሎ ቀዛፊዎች ወደ ጥልቁ ባሕር እንዳይወድቁ በፈሩ ጊዜ ሸራውን አወረዱ፤እንዲሁም እንድንሄድ አደረግን።
ሐዋርያት ሥራ 27:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋያማ በሆነ ቦታም እንዳይወድቁ ፈሩ፤ ስለዚህም ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቅ በባሕሩ ላይ ጣሉ፤ ፈጥኖ እንዲነጋም ጸለዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቋጥኞቹም ጋራ እንዳንላተም በመፍራት፣ አራት መልሕቆች ከመርከቡ በስተኋላ ጣሉ፤ ምነው በነጋ እያሉም ይለምኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተ ኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፤ ቀንም እንዲሆን ተመኙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መርከባችን በባሕሩ ዳር ካሉ ድንጋዮች እንዳይጋጭ ፈርተው ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቆችን ወደ ባሕሩ አወረዱ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ አልፎ ቀን እንዲመጣላቸው ይጸልዩ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፥ ቀንም እንዲሆን ተመኙ። |
ከዚህ በኋላ ተጋግዘን በገመድ አጠናከርናት፤ ከዚህም ቀጥሎ ቀዛፊዎች ወደ ጥልቁ ባሕር እንዳይወድቁ በፈሩ ጊዜ ሸራውን አወረዱ፤እንዲሁም እንድንሄድ አደረግን።
ከዚህ በኋላም ቀዛፊዎቹ ከመርከብ ሊኮበልሉ በወደዱ ጊዜ ወደ ኋላ ሊመለሱ ከምድር ላይ ሆነው መርከባቸውን የሚያጠናክሩ መስለው ጀልባቸውን ወደ ባሕር አወረዱ።
ከፈራህበት ከልብህ ፍርሀት የተነሣ፥ በዐይንህም ካየኸው የተነሣ፥ ሲነጋ እንዴት ይመሽ ይሆን? ትላለህ፤ ሲመሽም እንዴት ይነጋ ይሆን? ትላለህ።