ሐዋርያት ሥራ 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህንም ለመፈጸም ከሊቃነ ካህናት ሥልጣን ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ከተማ ሄድሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚህ መሠረት አንድ ቀን ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ በምጓዝበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህም ነገር ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ስሄድ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለዚሁ ጉዳይ ከካህናት አለቆች ሙሉ ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ እጓዝ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ነገ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ስሄድ፥ |
ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ በፈጸመ ጊዜ ካህናትና ነቢያተ ሐሰት፥ ሕዝቡም ሁሉ፥ “ሞትን ትሞታለህ” ብለው ያዙት።
ይህንም በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከሊቃነ ካህናትም ሥልጣን ተቀብዬ ከቅዱሳን ብዙዎችን ወደ ወኅኒ ቤት አስገባኋቸው፤ ሲገድሏቸውም አብሬ እመክር ነበርሁ።
ንጉሥ ሆይ፥ እኩል ቀን በሆነ ጊዜ በመንገድ ስሄድ ከፀሐይ ይልቅ የሚበራ መብረቅ በእኔና ከእኔ ጋር ይሄዱ በነበሩት ላይ ከሰማይ ሲያንፀባርቅ አየሁ።