ሐዋርያት ሥራ 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ይህንም በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከሊቃነ ካህናትም ሥልጣን ተቀብዬ ከቅዱሳን ብዙዎችን ወደ ወኅኒ ቤት አስገባኋቸው፤ ሲገድሏቸውም አብሬ እመክር ነበርሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በኢየሩሳሌምም ያደረግሁት ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብዬ ብዙ ቅዱሳንን አሳስሬአለሁ፤ በመገደላቸውም ተስማምቻለሁ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፤ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በኢየሩሳሌም ያደረግኹትም ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች በተቀበልኩት ሥልጣን ከምእመናን ብዙዎቹ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አድርጌአለሁ፤ ሲገድሉአቸውም ከገዳዮቻቸው ጋር ተስማምቻለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፥ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ። Ver Capítulo |