ሐዋርያት ሥራ 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ጭንቅ ከእጃችን ነጥቆ ወደ አንተ ላከው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የጦር አዛዡ ሉስዮስ መጥቶ በታላቅ ኀይል ከእጃችን ነጥቆ ወሰደው፤ ከሳሾቹም ወደ አንተ እንዲመጡ አዘዘ።] መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ኃይል ከእጃችን ወሰደው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የጦር አዛዡ ሉስዮስ መጥቶ በታላቅ ኀይል ከእጃችን ነጥቆ ወሰደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ኃይል ከእጃችን ወሰደው፥ |
ሊገድሉትም ፈልገው ብዙ ደበደቡት፤ ወዲያውም ኢየሩሳሌም በመላዋ እንደ ታወከች የሚገልጥ መልእክት ወደ ሻለቃው ደረሰለት።
እጅግም በታወኩ ጊዜ ጳውሎስን እንዳይነጥቁት የሻለቃው ፈራና መጥተው ከመካከላቸው አውጥተው ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ።
ከመቶ አለቆችም ሁለቱን ጠርቶ፥ “ከወታደሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረሰኞች፥ ሁለት መቶ ቀስተኞችም ምረጡ፤ ከሌሊቱም በሦስት ሰዓት ወደ ቂሣርያ ይሂዱ” አላቸው።