La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ጊዜ ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ከሕ​ዝብ ጋር በመ​ከ​ራ​ከር፥ ወይም በፍ​ጅት ሳይ​ሆን በመ​ቅ​ደስ ስነጻ አገ​ኙኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዐት ፈጽሜ ይህንኑ ሳደርግ አገኙኝ፤ የሕዝብ ሁካታ ወይም ረብሻ አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በቤተ መቅደስም ያገኙኝ ይህንኑ ሳደርግ ነው፤ በዚያን ጊዜ የመንጻትን ሥርዓት ፈጽሜ ነበር፤ ከእኔ ጋር ብዙ ሕዝብ አልነበረም፤ ሁከትም አልተነሣም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 24:18
7 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ እኔን ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ? የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን የሰ​ሙ​ኝን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እኔም የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እነሆ፥ እነ​ርሱ ያው​ቃሉ።”


እኛ በተ​ወ​ለ​ድ​ን​በት በጳ​ርቴ፥ በሜድ፥ በኢ​ላ​ሜጤ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል፥ በይ​ሁዳ፥ በቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ በጳ​ን​ጦ​ስና በእ​ስያ፥


ይዘ​ሃ​ቸው ሂድ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ራስ​ህን አንጻ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ላጩ ስለ እነ​ርሱ ገን​ዘብ ክፈ​ል​ላ​ቸው፤ የሚ​ያ​ሙ​ህም በሐ​ሰት እንደ ሆነ፥ አን​ተም የኦ​ሪ​ትን ሕግ እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ ሁሉም ያው​ቃሉ።


በም​ኵ​ራብ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ቢሆን፥ በከ​ተ​ማም ቢሆን ሕዝ​ብን ሳውክ፥ ከማ​ንም ጋር ስከ​ራ​ከር አላ​ገ​ኙ​ኝም።


ሰለ​ዚ​ህም ብቻ አይ​ሁድ በመ​ቅ​ደስ ያዙኝ፤ ሊገ​ድ​ሉ​ኝም ወደዱ።


የነጻ ወጭ​ዎች ከም​ት​ባ​ለው ምኵ​ራ​ብም ከቀ​ሬ​ናና ከእ​ስ​ክ​ን​ድ​ርያ፥ ከቂ​ል​ቅ​ያና ከእ​ስያ የሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ይከ​ራ​ከ​ሩት ነበር።