ጳውሎስም በእስያ እንዳይዘገይ በኤፌሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚቻለውም ቢሆን ለበዓለ ኀምሳ ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኵሎ ነበርና።
ሐዋርያት ሥራ 24:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ዓመታትም በኋላ ለወገኖች ምጽዋትንና መሥዋዕትን ላደርግ መጣሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከብዙ ዓመት በኋላም፣ ለድኻው ወገኔ ምጽዋትና መባ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም መጣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከኢየሩሳሌም ከወጣሁ ብዙ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ለወገኖቼ የሚሆን የእርዳታ ገንዘብና ለእግዚአብሔር የሚሰጥ መባ ይዤ መጣሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤ |
ጳውሎስም በእስያ እንዳይዘገይ በኤፌሶን በኩል ሊሄድ ቈርጦ ነበር፤ የሚቻለውም ቢሆን ለበዓለ ኀምሳ ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኵሎ ነበርና።
ያንጊዜም ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር ነጻ። የመንጻታቸውንም ወራት መድረሱን ከነገራቸው በኋላ ሁሉም እየአንዳንዳቸው መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ይዞአቸው ገባ።
ይኸውም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳንን በአገልግሎቴ ደስ አሰናቸው ዘንድ በይሁዳ ሀገር ካሉ ዐላውያን እንዲያድነኝ ነው።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸርነቱን ታውቃላችሁ፤ በእርሱ ድህነት እናንተ ባለጸጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለጸጋ ሲሆን፥ ስለ እናንተ ራሱን ድሃ አደረገ።
ይህቺ የዚህ ሥራ አገልግሎት ግዳጅ የምትፈጽመው ለዚህ ለቅዱሳን ችግር መሟላት ብቻ አይደለም፤ በቅዱሳን ዘንድም ደግሞ የእግዚአብሔርን ምስጋና ታበዛለች።