የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው ተከትዬ፥ ሁሉንም በየተራው እውነተኛውን እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሁኖ ታየኝ።
ሐዋርያት ሥራ 23:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከሉስዮስ ቀላውዴዎስ፥ ለክቡር አገረ ገዢ ፊልክስ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቀላውዴዎስ ሉስያስ፤ ለክቡር አገረ ገዥ ለፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ ወደ ክቡር አገረ ገዢው ወደ ፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፤ ለክቡር አገረ ገዢ ፊልክስ! ሰላም ለአንተ ይሁን! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ ወደ ክቡር አገረ ገዡ ወደ ፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን። |
የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው ተከትዬ፥ ሁሉንም በየተራው እውነተኛውን እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሁኖ ታየኝ።
እንዲህ የምትል መልእክትም በእጃቸው ጻፉ፤ “ከሐዋርያትና ከቀሳውስት ከወንድሞችም በአንጾኪያ፥ በሶርያና በኪልቅያ ለሚኖሩ፥ ከአሕዛብ ላመኑ ወንድሞቻችን ትድረስ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ ደስ ይበላችሁ።
ከዚህም በኋላ ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢውም ደረሱ፤ የተላከውንም ደብዳቤ ለአገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳውሎስንም ወደ እርሱ አቀረቡት።
“ክቡር ፊልክስ ሆይ፥ በዘመንህ ብዙ ሰላምን አግኝተናል፤ በጥበብህም በየጊዜው በየሀገሩ የሕዝቡ ኑሮ የተሻሻለ ሆኖአል፤ ሥርዐትህንም በሁሉ ዘንድ ስትመሰገን አግኝተናታል።