La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባለፈባቸውም ስፍራዎች ሕዝቡን በብዙ ቃል እየመከረ ግሪክ አገር ደረሰ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእነዚያ በሚያልፍባቸው ስፍራዎች ምእመናንን በብዙ ምክር እያበረታታ ወደ ግሪክ አገር ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 20:2
17 Referencias Cruzadas  

ይሁዳን ለእኔ ገትሬአለሁ፣ ቀስቱን በኤፍሬም ሞልቼአለሁ፣ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ አንቺንም እንደ ኃያል ሰው ሰይፍ አደርግሻለሁ።


ሕዝ​ቡ​ንም ይገ​ስ​ጻ​ቸ​ውና በሌ​ላም በብዙ ነገር የም​ሥ​ራች ይነ​ግ​ራ​ቸው ነበር።


የደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም ልቡና አጽ​ናኑ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም እን​ዲ​ጸኑ፦“ በብዙ ድካ​ምና መከራ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እን​ገባ ዘንድ ይገ​ባ​ናል” እያሉ መከ​ሩ​አ​ቸው።


በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅ​ያም እየ​ዞረ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን አጽ​ናና።


ከዚ​ያም ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሄድን፤ ይህ​ች​ውም የመ​ቄ​ዶ​ንያ ዋና ከተ​ማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበ​ረች፤ በዚ​ያ​ችም ሀገር ጥቂት ቀን ሰነ​በ​ትን።


አን​ፊ​ጶ​ልና አጶ​ሎ​ንያ ወደ​ሚ​ባሉ ሀገ​ሮ​ችም ሄዱ፤ የአ​ይ​ሁድ ምኵ​ራብ ወደ አለ​በት ወደ ተሰ​ሎ​ን​ቄም ደረሱ።


ወን​ድ​ሞች ግን ጳው​ሎ​ስ​ንና ሲላ​ስን በሌ​ሊት ወደ ቤርያ ሸኙ​አ​ቸው፤ ወደ​ዚ​ያም በደ​ረሱ ጊዜ ወደ አይ​ሁድ ምኵ​ራብ ገቡ።


ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።


ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሰገ​ነት ወጣ፤ ማዕ​ዱ​ንም ባርኮ በላ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብዙ ትም​ህ​ርት አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚያ በኋ​ላም ተነ​ሥቶ ሄደ።


በዚ​ያም ሦስት ወር ተቀ​መጠ፤ ወደ ሶር​ያም በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ ዐስቦ ሳለ አይ​ሁድ ስለ ተማ​ከ​ሩ​በት ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሊመ​ለስ ቈረጠ።


እን​ኪ​ያስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ ፈጥኜ እመ​ጣ​ለሁ፤ ነገር ግን የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ነገር አል​ሻም፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውን እሻ​ለሁ እንጂ።


እር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ፍጹም የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው እና​ቀ​ር​በው ዘንድ፥ እኛ የም​ና​ስ​ተ​ም​ር​ለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የም​ን​ጠ​ራ​ለ​ትና የም​ን​ገ​ሥ​ጽ​ለት፥ ሥራ​ው​ንም በጥ​በብ ሁሉ የም​ን​ና​ገ​ር​ለት ነው።


ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና።


ልመናችን ከስሕተት ወይም ከርኵሰት ወይም ከተንኰል አልነበረምና፤


እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።