Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 20:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሁከቱም እንደ በረደ፣ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርትን አስጠርቶ መከራቸው፤ ተሰናብቷቸውም ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፤ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሁከቱ ጸጥ ካለ በኋላ ጳውሎስ ምእመናኑን በአንድነት አስጠርቶ በምክር ቃል አጽናናቸው፤ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፥ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 20:1
20 Referencias Cruzadas  

ወደ መቄ​ዶ​ን​ያም በደ​ረ​ስን ጊዜ ለሰ​ው​ነ​ታ​ችን ጥቂት ስን​ኳን ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ንም፤ በሁ​ሉም መከራ አጸ​ኑ​ብን እንጂ፤ በው​ጭም መጋ​ደል ነበር፤ በው​ስ​ጥም ፍር​ሀት ነበር።


ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ በመ​ቄ​ዶ​ን​ያና በአ​ካ​ይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚ​ያም ከደ​ረ​ስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገ​ባ​ኛል” አለ።


ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።


ከወንድሞች ሁሉ ጋር በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ በተ​ቀ​ደ​ሰች ሰላ​ምታ እርስ በር​ሳ​ችሁ ሰላም ተባ​ባሉ።


መቄ​ዶ​ን​ያም ደርሼ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በመ​ቄ​ዶ​ንያ በኩል አል​ፋ​ለ​ሁና።


እርስ በር​ሳ​ችሁ በተ​ቀ​ደሰ ሰላ​ምታ ሰላም ተባ​ባሉ፤ የክ​ር​ስ​ቶስ ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ሰላም ይሉ​አ​ች​ኋል።


ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት።


ጳው​ሎ​ስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፤ አቅ​ፎም ያዘው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ “ነፍሱ አለ​ችና አት​ደ​ን​ግጡ” አላ​ቸው።


ለጳ​ው​ሎ​ስም በሌ​ሊት አንድ መቄ​ዶ​ናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄ​ዶ​ንያ ዕለ​ፍና ርዳን” እያለ ሲማ​ል​ደው በራ​እይ ተገ​ለ​ጸ​ለት።


በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም።


በተ​ቀ​ደሰ ሰላ​ምታ እርስ በር​ሳ​ችሁ ሰላም ተባ​ባሉ፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ እን​ዴት ናችሁ? ይሏ​ች​ኋል።


ከዚ​ያም ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሄድን፤ ይህ​ች​ውም የመ​ቄ​ዶ​ንያ ዋና ከተ​ማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበ​ረች፤ በዚ​ያ​ችም ሀገር ጥቂት ቀን ሰነ​በ​ትን።


በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ።


በዚ​ያም ሦስት ወር ተቀ​መጠ፤ ወደ ሶር​ያም በመ​ር​ከብ ለመ​ሄድ ዐስቦ ሳለ አይ​ሁድ ስለ ተማ​ከ​ሩ​በት ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሊመ​ለስ ቈረጠ።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios