የተሰጣቸውን ወይፈንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበዓልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ የሠሩትንም መሠዊያ እያነከሱ ይዞሩ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 19:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁዳዊ እንደሆነም ባወቁ ጊዜ “የኤፌሶን አርጤምስ ክብርዋ ታላቅ ነው” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ሁሉም በአንድ ድምፅ ጮሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እርሱ አይሁዳዊ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁዳዊ ግን እንደሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ “የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እስክንድር አይሁዳዊ መሆኑን ሰዎቹ ሁሉ ባወቁ ጊዜ “የኤፌሶን አርጤሚስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያኽል ሁሉም በአንድ ድምፅ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁዳዊ ግን እንደ ሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። |
የተሰጣቸውን ወይፈንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበዓልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ የሠሩትንም መሠዊያ እያነከሱ ይዞሩ ነበር።
በዚያም ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ለአርጤምስም ከብር የቤተ መቅደስ ምስል ይሠራ ነበር፤ አንጥረኞችንም እያሠራ ብዙ ገንዘብ ይሰጣቸው ነበር።
አሁን ግን እንደምታዩትና እንደምትሰሙት ይህ ጳውሎስ ኤፌሶንን ብቻ ሳይሆን መላውን እስያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝብንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚሠሩትንም ሁሉ አማልክት አይደሉም አላቸው።
በዚያ የነበሩ አይሁድም እስክንድሮስ የሚባል አይሁዳዊ ሰውን ከመካከላቸው አስነሡ፤ እርሱም ተነሥቶ በእጁ ምልክት ሰጠና ለሕዝቡ ሊከራከርላቸው ወደደ።
ከዚህም በኋላ የከተማው ጸሓፊ ተነሥቶ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤፌሶን ከተማ ታላቂቱን አርጤምስንና ከሰማይ የወረደውን ጣዖትዋን እንደምትጠብቅ የማያውቅ ማነው?
አታመንዝሩ ትላለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመነዝራለህ፤ ወደ ጐልማሳ ሚስትም ትሄዳለህ፤ ጣዖትን ትጸየፋለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህ።
ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።