La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሥራ​ቸው አንድ ስለ ነበረ ድን​ኳን ሰፊ​ዎ​ችም ስለ ነበሩ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብሮ ኖረ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይሠሩ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም እንደ እነርሱ ድንኳን ሰፊ ስለ ነበረ፣ ከእነርሱ ጋራ ተቀምጦ በተመሳሳይ ሥራ ላይ ተሰማራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእርሱ ሥራ ልክ እንደ እነርሱ ድንኳን መስፋት ስለ ነበር ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ አብሮአቸው ይሠራ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 18:3
13 Referencias Cruzadas  

ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም እን​ሂድ፤ ከእ​ኛም እያ​ን​ዳ​ንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፥ የም​ና​ድ​ር​በ​ትም ቤት እን​ሥራ፥” አሉት፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ” አለ።


በእ​ጃ​ችን ሥራ እያ​ገ​ለ​ገ​ልን እን​ደ​ክ​ማ​ለን፤ ይረ​ግ​ሙ​ናል፤ እኛ ግን እን​መ​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ ያሳ​ድ​ዱ​ናል፤ እኛ ግን እን​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ እን​ታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለ​ንም።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲሁ ወን​ጌ​ልን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሰዎች ለሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው መተ​ዳ​ደ​ሪያ በዚ​ያው ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ይሆን ዘንድ አዘዘ።


እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል።


እን​ግ​ዲህ ዋጋዬ ምን​ድን ነው? ወን​ጌ​ልን ባስ​ተ​ም​ርም በሹ​መቴ የማ​ገ​ኘው ሳይ​ኖር ወን​ጌ​ልን ያለ ዋጋ እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ባደ​ርግ ነው።


ወይስ ራሴን በሁሉ ያዋ​ረ​ድሁ በደ​ልሁ ይሆን? እና​ንተ ከፍ ከፍ ትሉ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወን​ጌል ያለ ዋጋ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።


እከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ ዘንድ ወደ እና​ንተ ካለ​መ​ም​ጣቴ በቀር፥ ከአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ ያሳ​ነ​ስ​ኋ​ችሁ በም​ን​ድን ነው? ይህ​ቺን በደ​ሌን ይቅር በሉኝ።


ወንድሞች ሆይ! ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋል፤ ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን እየሠራን፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን።