ሐዋርያት ሥራ 17:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና እኛም ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ልንረዳ እንወዳለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በጆሯችን የምታሰማን እንግዳ ነገር ስለ ሆነብን፣ ምን ማለት እንደ ሆነ ማወቅ እንፈልጋለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ እንግዳ ነገሮችን አሰምተኸናል፤ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ማወቅ እንፈልጋለን።” |
ጴጥሮስም ስለ አየው ራእይ ምን እንደ ሆነ ሲያወጣና ሲያወርድ ከቆርኔሌዎስ ተልከው የመጡ ሰዎች የስምዖንን ቤት እየጠየቁ በደጅ ቁመው ነበር።
ይዘውም አርዮስፋጎስ ወደሚባል ሸንጎ ወሰዱት፤ እንዲህም አሉት፥ “ይህን የምታስተምረውን አዲስ ትምህርት እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? እስቲ ንገረን?
የአቴና ሰዎችና በዚያም የነበሩ እንግዶች ሁሉ አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር ሌላ ዐሳብ አልነበራቸውም።
ለሥጋዊ ሰው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ይመስለዋልና፥ አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቅ አይችልም።