Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ይዘ​ውም አር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ወደ​ሚ​ባል ሸንጎ ወሰ​ዱት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን የም​ታ​ስ​ተ​ም​ረ​ውን አዲስ ትም​ህ​ርት እና​ውቅ ዘንድ ይቻ​ለ​ና​ልን? እስቲ ንገ​ረን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይዘውም አርዮስፋጎስ ወደተባለው ስፍራ በመውሰድ እንዲህ አሉት፤ “አንተ የምታስተምረው ይህ አዲስ ትምህርት ምን እንደ ሆነ እንድናውቅ ትፈቅዳለህን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19-20 ይዘውም “ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን፤” ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ስለዚህ ጳውሎስን ይዘው አርዮስፋጎስ በተባለው ስፍራ ወደሚሰበሰበው ጉባኤ አመጡትና እንዲህ አሉት፤ “ይህ አንተ የምታስተምረው አዲስ ትምህርት ምን እንደ ሆነ ማወቅ እንችላለንን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19-20 ይዘውም፦ ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 17:19
12 Referencias Cruzadas  

ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።


ጳው​ሎ​ስም በአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ውስጥ ቆሞ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የአ​ቴና ሰዎች! በሥ​ራ​ችሁ ሁሉ አማ​ል​ክ​ትን ማም​ለክ እን​ደ​ም​ታ​በዙ አያ​ች​ኋ​ለሁ።


አግ​ሪ​ጳም ጳው​ሎ​ስን፥ “ስለ ራስህ ትና​ገር ዘንድ ፈቅ​ደ​ን​ል​ሃል” አለው፤ ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎስ እጁን አነ​ሣና ይነ​ግ​ራ​ቸው ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦


አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “እኔም ያን ሰው ልሰ​ማው እወ​ዳ​ለሁ” አለው፤ ፊስ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ ነገ ትሰ​ማ​ዋ​ለህ” አለው።


ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ ፊል​ክስ ከአ​ይ​ሁ​ዳ​ዊት ሚስቱ ከድ​ሩ​ሲላ ጋር መጣ። ልኮም ጳው​ሎ​ስን አስ​ጠ​ራው፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ ማመ​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሰማው።


በጆ​ሮ​አ​ችን እን​ግዳ ነገር ታሰ​ማ​ና​ለ​ህና እኛም ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ልን​ረዳ እን​ወ​ዳ​ለን።”


“እርስ በር​ሳ​ችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእ​ዛዝ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ እንደ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተዋ​ደዱ።


ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።


አም​ነው የተ​ከ​ተ​ሉት ሰዎ​ችም ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ከአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ወገን የሚ​ሆን ዲዮ​ና​ስ​ዮስ ነበር፤ ደማ​ሪስ የም​ት​ባል ሴትም ነበ​ረች፤ ሌሎ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ።


የሻ​ለ​ቃ​ውም ልጁን በእጁ ይዞ ለብ​ቻው ገለል አድ​ርጎ፥ “የም​ት​ነ​ግ​ረኝ ነገሩ ምን​ድ​ነው?” አለው።


ጕበ​ኛ​ውም፥ “ይነ​ጋል፤ ደግ​ሞም ይመ​ሻል፤ ትጠ​ይቁ ዘንድ ብት​ወ​ድዱ ጠይቁ፤ ተመ​ል​ሳ​ች​ሁም ኑ፥” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios