በእስጢፋኖስ ሞት ምክንያት የተበተኑት ግን፤ ወደ ፊንቄ ወደ ቆጵሮስና ወደ አንጾኪያ ደረሱ፤ ቃሉንም ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለአንድስ እንኳ አይናገሩም ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወንጌልን ሰበኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ወንጌልን መስበክ ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ወንጌልን ሰበኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር። |
በእስጢፋኖስ ሞት ምክንያት የተበተኑት ግን፤ ወደ ፊንቄ ወደ ቆጵሮስና ወደ አንጾኪያ ደረሱ፤ ቃሉንም ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለአንድስ እንኳ አይናገሩም ነበር።
እንዲህም አሉአቸው፥ “እናንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? እኛስ እንደ እናንተ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን፥ ባሕርንም በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እናስተምራችኋለን።
በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰበኩ፤ ብዙ ሰዎችንም ደቀ መዛሙርት አድርገው ወደ ልስጥራን፥ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ።
ራእዩንም ባየ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ልንሄድ ወደድን፤ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር የሚጠራን መስሎናልና።
ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።