La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይዞም ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባው፤ ለሚ​ጠ​ብ​ቁት ለዐ​ሥራ ስድ​ስቱ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሳ​ልፎ ሰጠው፤ ከፋ​ሲ​ካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያ​ቀ​ር​በው ወድዶ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጴጥሮስን ወህኒ ቤት ካስገባው በኋላ፣ አራት አራት ወታደሮች እየሆኑ እንዲጠብቁት በአራት ፈረቃ ለተመደቡ ወታደሮች አስረከበው፤ ይህን ያደረገውም የፋሲካ በዓል ካለፈ በኋላ ሕዝብ ፊት አውጥቶ ሊያስፈርድበት ዐስቦ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው፤ ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጴጥሮስን ካስያዘ በኋላ ወደ ወህኒ ቤት አስገባው፤ ከአይሁድ የፋሲካ በዓል በኋላ ለሕዝቡ እስኪያቀርበው ድረስ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍሮች አስረከበው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 12:4
22 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


በሰው ልብ ብዙ ዐሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል።


ሜም። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ይመ​ጣል፥


“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።


ነገር ግን “በሕዝቡ ዘንድ ሁከት እንዳይነሣ በበዓል አይሁን፤” አሉ።


ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።


ከዚ​ህም ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ይይ​ዙ​አ​ች​ኋል፤ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ያስ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገ​ሥ​ታ​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት ይወ​ስ​ዱ​አ​ች​ኋል።


እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እኔ ለመ​ታ​ሰ​ርም ቢሆን፥ ለሞ​ትም ቢሆን እንኳ ከአ​ንተ ጋራ ለመ​ሄድ የተ​ዘ​ጋ​ጀሁ ነኝ” አለው።


ጭፍ​ሮ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በሰ​ቀ​ሉት ጊዜ ልብ​ሶ​ቹን ወስ​ደው ከጭ​ፍ​ሮቹ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት ክፍል አድ​ር​ገው መደ​ቡት፤ ቀሚ​ሱ​ንም ወሰዱ፤ ቀሚ​ሱም ከላይ ጀምሮ የተ​ሠራ ሥረ​ወጥ እንጂ የተ​ሰፋ አል​ነ​በ​ረም።


“እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ አንተ ጐል​ማሳ ሳለህ በገዛ እጅህ ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ወደ ወደ​ድ​ኸው ትሄድ ነበር፤ በሸ​መ​ገ​ልህ ጊዜ ግን እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፤ ወገ​ብ​ህ​ንም ሌላ ያስ​ታ​ጥ​ቅ​ሃል፤ ወደ​ማ​ት​ወ​ደ​ውም ይወ​ስ​ድ​ሃል።”


አይ​ሁ​ድ​ንም ደስ እን​ዳ​ላ​ቸው አይቶ ጴጥ​ሮ​ስን ደግሞ ያዘው፤ ያን​ጊ​ዜም የፋ​ሲካ በዓል ነበር።


ጴጥ​ሮ​ስ​ንም በወ​ኅኒ ቤት ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ዘወ​ትር ስለ እርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር።


እጅ​ህና ምክ​ርህ እን​ዲ​ደ​ረግ የወ​ሰ​ኑ​ትን ይፈ​ጽሙ ዘንድ።


እጃ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው ያዙ​አ​ቸው፤ ጊዜ​ዉም ፈጽሞ መሽቶ ነበ​ርና እስከ ማግ​ሥቱ ድረስ በወ​ኅኒ ቤት አገ​ቡ​አ​ቸው።


እጃ​ቸ​ው​ንም በሐ​ዋ​ር​ያት ላይ አነሡ፤ ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ በሕ​ዝቡ ወኅኒ ቤትም አስ​ገ​ቧ​ቸው።


ሳውል ግን ገና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ይቃ​ወም ነበር፤ የሰ​ው​ንም ቤት ሁሉ ይበ​ረ​ብር ነበር፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እየ​ጐ​ተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስ​ገ​ባ​ቸው ነበር።