ሐዋርያት ሥራ 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመዝሙር መጽሐፍ ‘መኖሪያዉ ምድረ በዳ ትሁን፤ በውስጧም የሚኖር አይኑር፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ’ ተብሎ ተጽፎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “በመዝሙር መጽሐፍ፣ ‘መኖሪያው ባድማ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይገኝ’ ደግሞም፣ ‘ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመዝሙር መጽሐፍ ‘መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይኑር፤’ ደግሞም ‘ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት፤’ ተብሎ ተጽፎአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህም የሆነበት ምክንያት በመዝሙር መጽሐፍ፥ ‘መኖሪያው ባዶ ይሁን፤ ማንም አይኑርበት፤ ደግሞም ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰድበት’ የሚል ተጽፎ ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመዝሙር መጽሐፍ፦ “መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን የሚኖርባትም አይኑር፤” ደግሞም፦ “ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት” ተብሎ ተጽፎአልና። |
እርሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ እንዳለው፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ የነገርኋችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላቸው።
“እናንተ ሰዎች ወንድሞቻችን ሆይ፥ ስሙ፤ ጌታችን ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባል።
በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ እንዳለ ኢየሱስን አስነሥቶ ተስፋውን ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል።