በእውነት ያመጣህልኝ አይደለም፤ አግባብስ በእውነት ታመጣልኝ ዘንድ ነበር። በደልህ፤ እንግዲህ ዝም በል፤ የወንድምህ መመለሻው ወደ አንተ ነው፤ አንተም ትሰለጥንበታለህ።”
3 ዮሐንስ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም በማኅበር ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ አንተ ስላለህ ፍቅር በቤተ ክርስቲያን ፊት መስክረዋል፤ በመንገዳቸውም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሠኝ ሁኔታ ብትረዳቸው መልካም ታደርጋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በቤተ ክርስቲያን ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳቸው መልካም ታደርጋለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ስለ አደረግህላቸው የፍቅር ሥራ በማኅበረ ምእመናን ፊት መስክረዋል፤ አሁንም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ በጒዞአቸው ብትረዳቸው መልካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ፤ |
በእውነት ያመጣህልኝ አይደለም፤ አግባብስ በእውነት ታመጣልኝ ዘንድ ነበር። በደልህ፤ እንግዲህ ዝም በል፤ የወንድምህ መመለሻው ወደ አንተ ነው፤ አንተም ትሰለጥንበታለህ።”
ለአማልክት የተሠዋውን፥ ሞቶ የተገኘውን፥ ደምንም አትብሉ፤ ከዝሙትም ራቁ፤ በራሳችሁ የምትጠሉትንም በወንድሞቻችሁ ላይ አታድርጉ፥ ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”
ከቤተ ክርስቲያንም በተላኩ ጊዜ ወደ ሰማርያና ወደ ፊንቄ ደርሰው አሕዛብ ወደ ሃይማኖት እንደ ተመለሱ ነገሩቸአቸው፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።
ከዚህም በኋላ ለመሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን።
ወደ አስባንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእናንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋላም ከእናንተ ወደዚያ እሄዳለሁ።
በእናንተም በኩል ወደ መቄዶንያ እንዳልፍ፥ ዳግመኛም ከመቄዶንያ እንድመለስና እናንተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸኙኝ ዘንድ መከርሁ።
ወደ እግዚአብሔር በሚገባችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ፥ እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰኙት ዘንድ።
ኀጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
ለድሜጥሮስ ሁሉ ይመሰክሩለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም ደግሞ እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችንም እውነት እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።