2 ሳሙኤል 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በእልልታ ቀንደ መለከት እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ባለ ሁኔታም ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት ሆይ እያሉና ቀንደ መለከቱን እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ ባለ ሁኔታም ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት እየጨፈሩና ቀንደ መለከቱን እየነፉ የጌታን ታቦት አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ዳዊትና መላው እስራኤል በደስታ እልል እያሉና የእምቢልታ ድምፅ እያሰሙ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ይዘው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደ መለከትም እየነፋ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡ። |
የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘምር አየችው፥ በልብዋም ናቀችው።
ዳዊትም በዜማ ዕቃ፥ በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን “ወንድሞቻችሁን ሹሙ” ብሎ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።
እንዲሁ እስራኤል ሁሉ በይባቤ፥ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም፥ በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።