ከመላው ነገደ እስራኤል የተሰበሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከሀገሩና ከመንግሥቱ ሸሸ።
2 ሳሙኤል 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከላይኛው መጋደያ መጣ፤ በዚያም መታቸውና፥ “ውኃ እንደሚያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን ፍልስጥኤማውያንን በፊቴ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “የላይኛው መጋደያ” ተብሎ ተጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት ወደ በኣልፐራሲም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፣ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፥ ጌታም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። በዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም ባዓል ፈራጺም ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ወርዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል ካደረገ በኋላ “እግዚአብሔር በጠላቶቼ መካከል እንደ ጐርፍ ሰባብሮ ገባ” አለ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “ባዓል ፈራጺም” ተብሎ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲም መጣ፥ በዚያም መታቸውና፦ ውኃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በፊቴ አፈረሳቸው አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲም ብሎ ጠራው። |
ከመላው ነገደ እስራኤል የተሰበሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከሀገሩና ከመንግሥቱ ሸሸ።
ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲን ወጣ፤ በዚያም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታቸው። ዳዊትም፥ “ውኃ እንዲያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲን ብለው ጠሩት።
እግዚአብሔርም በኃጥኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፤ በገባዖን ሸለቆም ይኖራል፤ ሥራውን ማለት መራራ ሥራውን በቍጣ ይሠራል፤ ቍጣውም ድንቅን ያደርጋል፤ መርዙም ልዩ ነው።