ኢዮአብም ንጉሡን፥ “የጌታዬ የንጉሡ ዐይን እያየ አምላክህ እግዚአብሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨምርበት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈልጋል?” አለው።
2 ሳሙኤል 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብና በሠራዊቱ አለቆች ላይ አሸነፈ። ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆችም የእስራኤልን ሕዝብ ይቈጥሩ ዘንድ ከንጉሥ ዘንድ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች ስላሸነፋቸው፣ የእስራኤልን ሰራዊት ለመመዝገብ ከፊቱ ወጥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም የንጉሡ ቃል ኢዮአብንና የሠራዊቱን አዛዦች አሸነፋቸው፤ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ለመቁጠር ከፊቱ ወጥተው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ግን ኢዮአብና የጦር መኰንኖቹ ትእዛዙን እንዲፈጽሙ ስላስገደዳቸው ከፊቱ ወጥተው የእስራኤልን ሕዝብ ለመቊጠር ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብና በሠራዊቱ አለቆች ላይ አሸነፈ። ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆችም የእስራኤልን ሕዝብ ይቆጥሩ ዘንድ ከንጉሥ ዘንድ ወጡ። |
ኢዮአብም ንጉሡን፥ “የጌታዬ የንጉሡ ዐይን እያየ አምላክህ እግዚአብሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨምርበት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈልጋል?” አለው።
ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጣ።
አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፤ የግብፅ ንጉሥም እንደ አዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው።
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር የወሰድህ እንደ ሆነ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሠፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።