Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ንጉሥ እንደ መሆኑ ኀይል አለ​ውና፤ ይህ​ንስ ለምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ማን ይለ​ዋል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የንጉሥ ቃል የበላይ ስለ ሆነ እርሱን፣ “ምን ታደርጋለህ?” ማን ሊለው ይችላል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና፥ “ይህንስ ለምን ታደርጋለህ?” ማን ይለዋል?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሥ ሁሉን ነገር ለማድረግ ሥልጣን አለው፤ “ለምን ይህን ሠራህ?” ብሎ የሚጠይቀውስ ማን አለ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና፥ ይህንስ ለምን ታደርጋለህ? ማን ይለዋል?

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 8:4
18 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የን​ጉሡ ቃል በኢ​ዮ​አ​ብና በሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ላይ አሸ​ነፈ። ኢዮ​አ​ብና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ይቈ​ጥሩ ዘንድ ከን​ጉሥ ዘንድ ወጡ።


በእ​ው​ነት፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በእ​ኔም ፋንታ በዙ​ፋኔ ላይ ይቀ​መ​ጣል ብዬ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማል​ሁ​ልሽ፥ እን​ዲሁ ዛሬ በእ​ው​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ።”


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በና​ያ​ስን ላከ፤ እር​ሱም አረ​ደው፤ ያን​ጊ​ዜም አዶ​ን​ያስ ሞተ።


ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን አዘ​ዘው፤ ወጥ​ቶም ገደ​ለው። የሰ​ሎ​ሞ​ንም መን​ግ​ሥት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና።


ንጉ​ሡም ዳር​ዮስ እንደ ላከው ቃል፥ በዚ​ያን ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ ያለ ገዥ ተን​ት​ናይ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም እን​ዲሁ ተግ​ተው አደ​ረጉ።


እርሱ ቢያ​ርቅ የሚ​መ​ልስ ማን ነው? እር​ሱ​ንስ፦ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?


የግ​ብ​ፅም ንጉሥ አዋ​ላ​ጆ​ችን ጠርቶ፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ጋ​ችሁ? ወን​ዶ​ቹን ሕፃ​ና​ት​ንስ ለምን አዳ​ና​ችሁ?” አላ​ቸው።


የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው።


የንጉሥ ቍጣ ከአንበሳ ቍጣ አያንስም፤ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል።


ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos