“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ቀርበህ ስማኝ፤ እርሻውን፥ በውስጡም ያለውን ዋሻውን ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።”
2 ሳሙኤል 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርናም ዳዊትን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በፊቱ ደስ ያሰኘውን ወስዶ ያቅርብ፤ እነሆም፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚቃጠልም እንጨት የአውድማ ዕቃና የበሬ ዕቃ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፤ ለሚነድደውም ዕንጨት፣ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚነደውም ዕንጨት፥ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርናም “ንጉሥ ሆይ! አውድማውን ወስደህ በፈቀድከው ዐይነት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርብበት፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው ይቀርቡ ዘንድ እነሆ እነዚህ በሬዎች አሉ፤ ስለ ማገዶም ጉዳይ እነርሱ የሚጠመዱበት ቀንበርና የእህል መውቂያው እንጨት ሁሉ አለ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርናም ዳዊትን፦ ጌታዬ ንጉሡ እንደ ወደደ ወስዶ ያቅርብ፥ እነሆ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚቃጠልም እንጨት የአውድማ ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ። |
“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ቀርበህ ስማኝ፤ እርሻውን፥ በውስጡም ያለውን ዋሻውን ሰጥቼሃለሁ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼሃለሁ፤ ሬሳህን ቅበር።”
ከእርሱም ዘንድ ተመልሶ ሁለቱን በሬዎች ወስዶ አረዳቸው፤ ሥጋቸውንም በበሬዎቹ ዕቃ ቀቀለው፤ ለሕዝቡም ሰጣቸው፤ በሉም፤ እርሱም ተነሥቶ ኤልያስን ተከትሎ ሄደ፤ ያገለግለውም ነበር።
ዳዊትም ኦርናን፥ “በላዩ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ሽጥልኝ፤ መቅሠፍቱም ከሕዝቤ ይከለከላል” አለው።
በዚያም ተራራ አናት ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ አሳምረህ ሥራ፤ ሁለተኛዉንም በሬ ውሰድ፤ በዚያም በቈረጥኸው በማምለኪያ ዐጸዱ እንጨት ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው።
ሰረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኦሴዕ እርሻ መጣ፤ ታላቅም ድንጋይ በነበረበት በዚያ ቆመ፤ የሰረገላውንም ዕንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።